🔴"የካስከው አንተ የበደልኩት እኔ" - ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረጻድቅ | 💦 ሊደመጥ የሚገባ
HTML-код
- Опубликовано: 10 апр 2025
- የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፡፡ መጽሐፈ ነህምያ ፪፥፳(2፥20)
፦ የአባቶቻቸውን አሰረ ፍኖት የተከተሉት ታላቁ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ልክ እንደ አፄ ዘርአ ያዕቆብ እንደ አፄ አድያም ሰገድ ኢያሱ እርሳቸውም የቅድስት ሥላሴን ታቦት ማስተከል አሰቡ ።
፦ ይህን ሲያስቡ አንድ ገዳም የሚኖር ባህታዊ መጥቶ ከቤተ መንግስትዎ በስተቀኝ ባለው ተረተር ላይ ሦስት ነጫጭ ርግቦች መጥተው ሲያርፉ በራዕይ አይቻለውና መካነ ሥላሴ የሚል ፅሁፍ ያለበት ጽላት አስፈልገው በዚያ ቦታ ላይ በሥላሴ ስም ቤተ ክርስቲያን ያሰሩ ብሎ በሰው በሰው ከንጉሡ ጆሮ እንዲደርስ አደረገ ።
፦ ንጉሡም ታቦቱን ሲያስፈልጉ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በመናገሻ አውራጃ በአዲስ ዓለም ፉየታ በተባለው ቦታ ተገኘ ።
መካነ ሥላሴ ጽላቱ ከወግዳ ነው የመጣው ። ከግራኝ መሐመድ አስቀድሞ ወረይሉ ደሴ የነበረ ነው ። ኃላ ግራኝ ሲነሳ ይዘው ሸሽተው ካህናቱ ወግዳ ውስጥ አገቡት ።
፦ ንጉሡ መካነ ሥላሴ የሚለውን ታቦት አስመጥተው አሁን ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲያን ካለበት ቦታ ከእርሳቸው ቤተመንግስት በሰሜን በኩል የአዛዥ ዛማኔል እልፍኝን አስባርከው ታህሳስ 22 1883 ዓ.ም ከዚያ አስገቡት።
የሕንጻ ቤተክርስቲያኑን ስራ ያስጀመሩት በዛው ዓመት በሚያዚያ ወር ነው ። ንጉሠ ነገሥቱ በነገሡ በ25 ዓመት ከ7 ወር ከ20 ቀን በዘመነ ሉቃስ 1883 ዓ/ም በሚያዚያ ወር ተጀመረ ። ስራው በቅልጥፍና ተሰርቶ ሐምሌ 7 ቀን 1883 ዓ/ም ቅዳሴ ቤቱ ተከብሮ ታብቱን አስገቡት ። የቤተ ክርስቲያኑም ስም መካነ ሥላሴ ተባለ ።
፦ ታቦቱ ለ12አመት በተሰራው ቤተክርስቲያን ከቆየ በኃላ አሁን የሚታየውን ቤተክርስቲያን ንጉሱ አሰርተው በ1895 ዓ.ም መስከረም 7ቀን ታቦቱ እንዲገባ ተደረገ እና መስከረም 10 ቀን ደግሞ በዚሁ ቤተክርስቲያን ተቀፀል ፅጌ ንጉሡ ባሉበት ተከበረ ።
፦ ከዛን ጊዜ ጀምሮ እሰከ አሁን ድረስ የተቀፀል ፅጌ ( የአፄ መስቀል )በዓለ በዚህ ቤተክርስቲያ ይከበራል ።
፦ የመካነ ሥላሴ የመጀመሪያ አስተዳዳሪ መልአከ ብርሀን ወልደ ዮሐንስ የሚባሉ ሲሆን ታቦቱ ወደ አዲሱና በዘመናዊ መልክ ወደተሰራው ቤተ ክርስቲያን እስከሚሄድና የአስተዳዳሪ የማዕረግ ስም እስከሚሰጠው ድረስ የመጨረሻው አስተዳዳሪ ደግሞ አባ መልዕክቱ በኃላ ሊቀ ሥልጣናት የተባሉት ሁለተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ናቸው ።
፦ መካነ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አዲስ አበባ ውስጥ ቀደም ብለው ከተተከሉ አድባራትና ገዳማት መካከል በአሰራር ቅደም ተከተል 6ኛ ነው ። የጥንቱ መካነ ሥላሴ የዛሬው በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን ከተመሰረተበት ከ1883 ዓ/ም ጀምሮ እሰከ አሁን የ133 ዓመት እድሜ አስቆጥሯል ።
፦ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴም ልክ እንደ አባቶቻቸው የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንን ለማሳነጽ በማሰብ ቀድሞ አገልግሎት ይሰጥ የነበረውን መካነ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሰፋ ባለ እና ዘመናዊ በሚባል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎቱ እንዲቀጥል በማሰብ ታሕሣስ 15 ቀን 1924 ዓ/ም የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠው ስራውን አስጀመሩ በ5 አመቱ የጠላት ወረራ ስራው ቢቋረጥም ከድል በኃላ ጥር 7 ቀን በ1936 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱ በታላቅ ስነ ሥርዓት ተከብሮ መካነ ሥላሴ የነበረው ታቦት ወደ አዲሱ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን እንዲመጣ አደረጉ ።
፦ የደቀድሞውን ቤተክርስቲያን ደግሞ የቅዱስ ባለወልድ እና የአርባይቱ እንስሳን ታቦት አስገብተውበት እስከ ዛሬ መንፈሳዊ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ።
የመጀመሪያው የማስፋፊያ ስራ መጀመር
፦አዲሱ ቤተክርስቲያን ከአገልግሎት ብዛት የተነሳ ስለጠበበ በደቡብ ፣ በምዕራብ እና በሰሜን በኩል ፈርሶ በ1939 ዓ.ም የማስፋፊያ ስራ ተሰራለት ።የቤተ ክርስቲያኑም ቅርጻ ቅርጾችና ጌጣጌጥች ቀድሞ ከነበራቸው ሁናቴ ወይም ይዘት ልቀውና አሸብርቀው ተሠሩ ።
የሁለተኛው የማስፋፊያ ስራ
፦ አሁንም ከሚሰጠው የአገልግሎት ስፋት አንፃር በድጋሚ ስለጠጠበበ በ1957ዓ.ም የማስፋፍያ ስራው ተጀምሮ በ1960 ዓ.ም ጥር 7 ቀን በድጋሜ ተሰርቶ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ አሁን የምናየውንም ይዘት እና ቅርፅ ያዞ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተብሎ ተሰየመ ።
ካቴድራሉ ከአክሱም ጽዮን ቀጥሎ በሁለተኛነት የሚጠራ ። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የራሷን ፓትርያርክ መሾም ከጀመረችበት ከ1951 ዓ/ም ጀምሮ የቅዱሳን ፓትርያርኮች በዓለ ሲመት የሚፈፀምበት ። የብፁዓን ጳጳሳት የሚሾሙበት በሕይወት በሚያልፉም ጊዜ መካነ እረፍታቸው የተፈጸመበት ፤ የቀ/ኃይለ ሥላሴ ጨምሮ ጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ፣ የሀገር መሪዎች ፣ የጥበብ ሰዎች ፣ ፖለቲከኞች ... መካነ ረፍታቸው የሚገኝበት ትልቅ የቱሪዝም ቦታ ነው ።
፦ ይህ ካቴድራል በ1200 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሲሆን በወንበር እስከ 1500 ሰው ሲይዝ ያለወንበር እስከ 2500 ሰው እንደሚይዝ ይገመታል ።
ከስር በተጠቀሱት የተለያዩ አማራጮች👇👇👇
🔵 የወገን ፈንድ(በተለያዩ አማራጮች) ሊንክ ፡- www.wegenfund....
🔵በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በአቢሲኒያ ባንክ፣ በአዋሽ ባንክ፣ በንብ በንክ እና በዓባይ ባንክ ለዚሁ አገልግሎት በተከፈተው አጭር ቁጥር 7829
🔵በውጭ ሀገር ላላችሁ
👉CASHGO MOBILE APP በመጠቀም ከላይ በተጠቀሰው የአቢሲኒያ ባንክ አካውንት
👉የካቴድራሉን ድረ ገጽ WWW.EOTC-HTC.ORG ላይ DONATE የሚለውን በመክፈት
👉(GOFUNFME) የጎ ፈንድ ሚ ሊንክ :- www.gofundme.c...
☑️ከላይ ባሉት የተለያዩ አማራጮች በቀላሉ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።
🌅ሼር ሼር ሼር⚡️⚡️⚡️
#ethiopiaorthodox #ethiopia #histroy ##viral #holytrinity #travel #duet #news #news #press #release #ortodox_mezmur #ortodox #ethiopian #views #addisababa #youtube #how #howto #newsibket #views #history
Thanks you God bless you amen amen
❤ዝማሬ መላዕክትን ያሠማልን ❤
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
AmeenAmeen🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏😍😍😍😍😍😍😍😍😍
Amen amen amen 🙏
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
❤❤❤🎉🎉🎉🎉❤❤❤❤
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤